Previous session detected
Resume Quiz
ይህ የመለማመጃ የእውቀት ፈተና ለዲሲ ዲኤምቪ የእውቀት ፈተና ለመዘጋጀት ይረዳዎታል። የዲሲ የነጂዎቸን የእውቀት ፈተናን በስኬታማ ሁኔታ ለማለፍ የዲሲን የመንዳት(የአሽከርካሪዎች) ማንዋል ማጥናት ግዴታ ነው። ዋናውን የነጂዎች የአውቀት ፈተና ለመውሰድ የዲሰ ዲኤምቪ የአገልግሎት ማእከል ሲመጡ፣ ለእያንዳንዱ ለተወሰደው የነጂ እውቀት ፈተና $10 ክፍያ አለው። የነጂዎች የአውቀት ፈተና የሚታይ በእጅ የሚነካ (ተች ስክሪን) ወይም በጆሮ የሚሰማ(ኦድዮ)(ሄድፎን በመጠቀም) ተች ስክሪን ያለው በኮምፕወተር ላይ የሚወሰድ ነው። በጆሮ የሚሰማውን(ኦድዮ)የሚመርጡ ከሆነ፣ ፈተናውን ከመጀመሮ በፊት የዲኤምቪ ተወካዩን ያስታውቋቸው። በዚሀ የመለማመጃ ፈተና ላይ ያሉት ጥያቄዎች በደሲ ዲኤምቪ በሚወሰደው በዋናው የነጅዎች የእውቀት ፈተና ላይ ሊኖሩ ወይም ላይኖሩ ይችላል። ፈተናውን ለመወሰድ ዲኤምቪ ከመምጣቶ በፊት የዲሲን የመንዳት(የአሽከርካሪዎች) ማንዋሉን ሙሉ በሙሉ ማጥናት እንዳለቦት ያስታውሱ። የእውቀት ፈተናውን ለማለፍ 80% ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ነጥብ ማግኘት ያስፈልጋል። የእውቀት ፈተናውን በ12 ወራት ግዜ ውስጥ 6 ግዜ ከወደቁ፣ የመጀመሪያውን ፈተና ከወደቁበት በሃላ እስከ 12 ወራት ድረስ 7ኛውን ፈተና ለመውሰድ አይፈቀድሎትም።